admin11
ቲዩ, 06/16/2026 - 11:43
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ለሥራ ክፍት አደረጉ
ሆሳዕና ፣ ሰኔ 9 / 2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡
የሆሳዕና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውስጡ
6 ተቋማት የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ 20 የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣
የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ .
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣
የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ፣
ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
Image