admin11
Fri, 06/26/2026 - 10:54
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር በዱራሜ ከተማ
መሶብ - የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ከፈቱ።
ሆሳዕና ሰኔ 19 ፣ 2018 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ ር )
በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የተገነባውን መሶብ - የአንድ ማዕከል
በዛሬው እለት መርቀው ከፈቱ።
"መሶብ-የአንድ ማዕከል አገልግሎት " በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ
የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን
በመጠቀም አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም
በቀላሉ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችል
ተመላክቷል።
መሶብ - የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ስፍራ በ6 ተቋማት
20 አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተመልክቷል።
Image