የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አተገባበር በጠንካራ የአመራር ስርዓትና
በቅርብ ክትትል ተመርቷል፤ የተሻሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል:-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 3/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎችን የ2018 በጀት ዓመት
ዕቅድ አፈጻጸም በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ ገምግመዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንደገለጹት፣የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ
አተገባበር በጠንካራ የአመራር ስርዓትና በቅርብ ክትትል ተመርቷል፤
የተሻሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል።
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች
በተቀናጀ መንገድ መመራቱም በጥንካሬ የሚጠቀስ መሆኑንም
ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል።
ለተግባራቱ የተደረገው የድጋፍና የክትትል ሥራም የተጠናከረ መሆኑን ጠቅሰው፣
በሂደቱም በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋለል።
በሁሉም አካባቢዎች ሥራዎች በቅርብ ክትትል መመራታቸውን ያስታወቁት
ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የግልና የጋራ ጥረቶችን በማቀናጀት እና የታዩ ክፍተቶችን
በፍጥነት በማረም ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በምርታማነትና በገቢ ማሳደግ ረገድ ጉልህ ውጤቶች
መመዝገባቸውን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው(ዶ/ር) ጠቁመው፣ የህብረተሰቡ
ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን አስረድተዋል።
የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን አጀንዳ ማድረግ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣
የገቢ አቅምን በሙሉ መጠቀም፣ ኢኒሼቲቮችን ማጠናከር፣ ምርታማነትንና
የመረጃ ጥራትን ማሻሻል በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ፣ አመራሩና ሰራተኞች ሙሉ
ሰዓታቸውን ለሥራ እንዲያውሉ ማድረግ እንዲሁም የህዝቦችን አንድነት
ለማጠናከር ተከታታይነት ያላቸው ሥራዎችን ማከናወን ቀጣይ ትኩረት
የሚሹ ጉዳዮች ስለመሆናቸውም አስገንዝበዋል።