የክልሉመስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018
በጀትአመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ፤ የቀጣይ ጊዜ
ትኩረቶችንምአመላከተ
ሆሳዕና፣ ሐምሌ 4/2018 ፦ 42 ተኛ መደበኛ ,ስብሰባዉን ያካሄደው
የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል መስተዳደር ምክርቤት በክልሉ አስፈፃሚ
መስሪያቤቶች የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
ላይ ውይይትአድርጓል፤ የቀጣይ ጊዜ ትኩረቶችም ተመላክተዋል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች
የእቅድአፈጻጸም በሁሉም የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሰላምና ፀጥታ እና
የመልካምአስተዳደር ዘርፎች ውጤታማና አበረታች እንደነበር በሪፖርቱ
ተመላክቷል።
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዓመታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሁኔታን
በተመለከተ፣ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ወይም የኢኮኖሚ ዕድገት በ10.2
በመቶዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።
ጠቅላላ የክልሉ ዓመታዊ ምርትን በየክፍላተ ኢኮኖሚው አስመልክቶ
በግብርናው ዘርፍ 8.1 በመቶ እድገት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ
ተመልክቷል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ 21.8 በመቶ እድገት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን
በአገልግሎት ዘርፍ 10.5 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ
በሪፖርቱ ተገልጿል።
በግብርናው ዘርፍ የታረሰ መሬት አድጓል፣ የሰብል ምርትና ምርታማነት አድጓል፣
የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን መጨመሩ እንዲሁም
የአገልግሎትዘርፍ ዕድገትም መጨመሩ ተመላክቷል።