የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) መልዕክት
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወስዱ ተማሪዎች 97 ነጥብ
4 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን ማለፍ ችለዋል።
ይህ ውጤት የመማር _ማስተማሩን ሂደት በማጠናከር፣
የመማር _ማስተማር ስነ ዘዴውንና የፈተና አስተዳደር
ስርዓቱን በማሻሻል ፣ እና የተማሪዎች በራስ የመተማመን
ስነ ልቦና እንዲጎለብት በተሠራዉ ተከታታይ የትምህርት
ጥራት ችግሮችን የመቀልበስና የተማሪዎችን ውጤት የማሻሻል
ሥራ የመጣ ነው።
ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት
ሴክተሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራን፣
ተማሪዎች፣ የተማሪዎች ወላጆች፣ የየደረጃዉ የትምህርት አመራር
ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎችም አካላት፣ዉጤቱ እንዲመዘገብ
ላደረጋችሁት አሰተዋጽኦ በራሴ እና በክልሉ መንግስት ስም ምስጋናዬን
አቀርባለሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለትም እወዳለሁ።
የትምህርት ጥራትን እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመረዉ
ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ ።