Skip to main content

ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት እየተሰጠ

ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በትኩረት

እየሰራ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 15/2018፦ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕር ሄንሲቭ

ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ጋር ምክክር አድርገዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት

እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ

ነው ብለዋል።

የምንሰራው የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ ድህነትን ለማሸነፍ ነው

ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።


የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕር ሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ

ሆስፒታል በቅብብሎሽ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ ላደረጉ አካላት

ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል። 

የጤና ስራ አድጋሚና በህዝብ እርካታ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ርዕሰ

መስተዳድሩ ለዚህም የጤና ባለሙያዎችን እና የአመራሩን ቁርጠኝነት

ይጠይቃል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። 

በሆስፒታሉ በሚሰጠው አገልግሎት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ደረጃ በደረጃ

ለመፍታት ጥረት መደረግ እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የስልጠና እና የምርምር ስራዎች ለጤናው ዘርፍ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ

የላቀ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

Image