ጂኮ ፓርክ ክልሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከቱሪዝም
ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀብት ያሳድጋል:-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በተገኙበት የማዕከላዊ
ኢትዮጵያ ክልል ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፓርክን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ
በተከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የክልሉ መንግስት በሁሉም መስክ የላቀ የህዝብ
ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ስራዎች ላይ በትኩረት
እየተሰራ ነው ብለዋል።
ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ
እየተካሔደ ያለው ጥረት ስኬታማ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ
ጠቁመዋል።
የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ አብነት የሆነ ክልል ነው ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመድረኩ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የጂኮ ፓርኩ እውን
መሆን ክልሉን እና ሀገሪቱን በማስተዋወቅ ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል።
የጎብኚዎችን ፍሰት በመጨመር የቱሪዝም ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ
የኢኮኖሚ አቅምን ያሳድጋል።
ለሆቴል ኢንዱስትሪ ማደግ የሚኖረው አበርክቶ የላቀ ሲሆን ለተለያዩ
ለምርምር እና ለጥናት ስራዎች ማዕከል በመሆን እንደሚያገለግልም
ተመላክቷል።
ጂኦ ፓርኩ አለም አቀፍ እውቅና ስለሚኖረው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እና
ኢኒሼቲቮች መነሻ ስለመሆኑም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የባህል እሴቶቻችን ይበልጥ ከማስተዋወቅ ባለፈ ለህብረተሰቡ የተቀናጀ
የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል።