በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል
የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ ድል መቀየር ተችሏል :- ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻውጣሰው (ዶር)
ሆሳዕና፣ሐምሌ 22/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 በጀት
ዓመት የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም እና በ2019 በጀት
አመት ዕቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ክልል አቀፍ የከፍተኛ
አመራሮች መድረክ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶር)
በምክክር መድረኩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት የባለፉት
3 ዓመታት ጉዞ በበርካታ ድሎች እና ፈተናዎች የታጀበ ነበር ብለዋል።
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል
የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ ድል መቀየር ተችሏል መቻሉን ርዕሰ
መስተዳድሩ አስረድተዋል።
ክልሉ ሲመሰረት የተደበላለቁ አመለካከቶች፣የእዳ ጫና ፣የሀብት እጥረት፣
የሀሰተኛ ሚዲያዎች መበራከት፣ደመወዝ በአግባቡ መክፈል ያለመቻ እና
ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውን ርዕሰ መስተዳደሩ አብራርተዋል።
ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በውስጥ አቅም በመፍታ ለተጨማሪ ድሎች በትኩረት
እየተሰራ ነው ብለዋል።
አዲስ ክልል ብንሆንም አጭሩንም ረጅሙንም ሩጫ ለማጠናቀቅ በቂ ስልት
በመንደፍ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት፣የተሞክሮ ማዕከል፣ የተረጋጋና
ሰላማዊ ክልል መፍጠር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው
አመላክተዋል።
ክልሉ የህብረ ብሔራዊነት ተምሳሌት እንዲሆን በተሟላ መንገጥ ወደ ተግባር
መገባቱን ምርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
በክልሉ በሁሉም መስክ በርካታ ስኬታማ ስራዎች መኖራቸውን መገንዘብ
ተችሏልያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2018 በጀት ዓመት መደበኛ የመንግስት፣
የፓርቲ እንዲሁም የምርጫ ስራን በስኬት መፈጸም ስለመቻሉም ርዕሰ
መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
የተለያዩ ደባል አጀንዳዎች በመኖራቸው ባሰብነው ፍጥነት መሰረት መጓዝ
እንዳንችል አድርጎናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ የነጠላ ትርክት መበራከት፣
በመዋቅሮች እና በሴክተሮች የአፈጻጸም ልዩነት መኖር እንዲሁም የስልጣን አተያይ
ችግሮችን ጠቁመዋል።
ያጋጠሙ ችግሮችን በአግባቡ በመገምገም ማስተካከል እንደሚገባም
ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
በክልሉ በመንግስት እና በፓርቲ ስራዎች ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና በአፈጻጸም
ረገድ የተስተዋሉ ውስንነቶችን ማረም የሚያስችል መድረክ ነው ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጋራ ተግባቦት ይፈጠራል ብለዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ ፣ የባለፉት 3 አመታት ጉዞ እና የባለፉት
አምስት ዓመታት የምርጫ ዘመን ማጠቃለያ ሀሳቦች ላይ ምክክር እንደሚደረግም
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።