የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል ዘመናትን የተሻገረ ነው :-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ነሐሴ 27/2018፦ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ልኡካን ቡድን በጽ/ቤታቸው አቀባበል አደረጉ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት
የረጅም ዘመናት ታሪክ አለው ብለዋል።
የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ሂደት ዘመናትን የተሻገረ ነው ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩ በተለይ በአድዋ ታሪክ ወጣቶች እና ሴቶች ከፍተኛ ድርሻ
እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።
ሴቶች ቀለብ ማዘጋጀት ወጣቶች ደግሞ በአርበኝነት ሀገርን የማዳን ትግል
ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
ወጣቶች ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ በማድረግ በሀገር እድገት ላይ
የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል።
ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ
ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
ወጣቶች ለህዝቦች አንድነት እና ትስስር በጋራ መስራት እንዳለባቸው
የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጉዞ
ማጠናከር ይጠበቃል ሲሉም አብራርተዋል።
ክልሉ በአጭር ጊዜ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በርካታ አብነታዊ
ስራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ስራ ማስጀመር
መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት
በስድስት ወራት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያደገ ስለ
መምጣቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።