Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ በልዩ ትኩረት 

የሚመሩ ተግባራት አፈጻጸም በጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው 

ሆሳዕና፣መስከረም 7 / 2019፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ትኩረት 

የሚመሩ ተግባራትን አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በግብርና፣በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣

በፋይዳ፣በኢትዮ ኮደርስ፣በገቢ፣በስራ እድል ፈጠራ፣በንግድ፣በመሬት 

አስተዳደር፣የከተማ እና የገጠር ኮሪደር ስራዎች ሪፖርት ላይ ዝርዝር 

ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል። 

እያንዳንዱ ስራ ያለበት ደረጃ፣የአፈጻጸም ሁኔታ፣እንዲሁም ስራዎች እንዴት 

እየተመሩ እንደነበር የአፈጻጸም ግምገማው የትኩረት መስኮች መሆናቸውን 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል። 

እንደ ክልል የሚሰጡ አቅጣጫዎች እና ግብረ መልሶችን መሰረት ያደረገ አፈጻጸም 

ላይ በዝርዝር ውይይት እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

Image