ህብረ-ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ሁለንተናዊ ሉአላዊነቷ
የተከበረ የማትበገር ሀገር መገንባት ይጠበቅብናል:-
ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣መስከረም 23/2019 ዓ.ም ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች
ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት
(ዶ/ር) እንደገለጹት በምክር ቤቱ ፊት ቆሜ የተሰጠኝን የህዝብ
አደራ እና ኃላፊነት በከፍተኛ ትህትና በጥልቅ አክብሮት እና
በንጹህ የአገልጋይነት ስሜት ነው ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ፣መንግስት እና የክልሉ ህዝቦች ለጣሉብኝ እምነት
እና ለተሰጠኝ ኃላፊነት አክብሮታዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
ህዝቦቿም እንዲሁ ታላቅ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የአኩሪ ታሪክ፣ቅርስ፣ባህል፣ትውፊት፣የእምነት፣የድንቅ ማንነት፣
የበርካታ የገጸ ምድር እና የገጸ ምድር ኃብት ባለቤት ስለመሆናችን
ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።
ፈጣሪ የቸረንን አቅም፣ጉልበት እና ጸጋ ወደ ሀገራዊ ጥቅም በመቀየር
የባህር በር ጥያቄአችንን እልባት ሰጥተን የህዝባችንን ሁለንተናዊ
ብልጽግናን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን ስልጣኔ መልሰን መገንባት እና
ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ይኖርብናል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ግልጽ ራዕይ አለው
ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ሁለንተናዊ
ሉአላዊነቷ የተከበረ የማትበገር፣በስፋት የምታመርት፣የጸናች ኢትዮጵያን
መገንባት ነው ብለዋል።
የክልላችን መንግስት ራዕይ እና ተልዕኮ የዚሁ ነጸብራቅ ስለመሆኑም
ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።