Skip to main content

ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን ምሶሶ የወል ምልክታችን 

ነው ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

ጥቅምት ፣ 2 /2019 ዓ.ም ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የትምጌታአስራት ዶ/ር በተኙበት 19 ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን 

ተከበረ

በአዲሱ የመደመር መንግሥት ምርሰረታ ማግስት እየተከበረ 

የሚገኘው 19ኛውየብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን 

ለብሔራዊመግባባትና ለአንድነታችን"በሚል መርህ በልዩ ድምቀት 

በማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል ተከብሯል።

ሰንደቅ ዓላማችን ሀገርን ወካይ አርማና መገለጫችን ከማድረግ ባለፈ 

ዜጎችበልዩ አክብሮትና ጥልቅ ፍቅር የሚመለከቱት የጋራ መገለጫችን 

ነው ሲሉ ርዕሰመስተዳድሩ ተደምጠዋል።

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን ምሰሶና የወል ምልክታችን 

በመሆንለወል ትርክት ግንባታ መሠረት ሆኖ የሚያገለግል ከወል እውነቶች 

መካከልአንዱ ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተደምጠዋል።

ሀገርን ወካይ፣ አርማና መገለጫ ከማድረግ ባለፈ ዜጎች በልዩ አክብሮትና በጥልቅ 

ፍቅርውስጥ ሆነው የጋራ መገለጫ አድርገው የሚያከብሩት ታላቅ ቀን መሆኑን 

ርዕሰመስተዳድሩ አስታውሰዋል።

ቀደምት ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የውጭ ኃይሎች ጋር በተለያዩ ዘመናት 

የተጋረጡባቸውንየየዘመኑን ፈተናዎች እንደየ ወቅቱ ሁኔታ ተፋልመው 

የሀገርንሉዓላዊነት አስከብረው ማለፋቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰው፤

የብሔራዊ ክብርና የሀገር ፍቅር የፈጠረው የአላማ ፅናት ላይ ቆመው ከፍተኛ 

መስዋዕትነትከፍለው ሉዓላዊነታ የተከበረ ሀገር አስረክበውናል ሲሉ የትምጌታ 

አስራት (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የዘመኑ አርበኛ የምግብ ሉዓላዊነትቷ የተረጋገጠ ለማድረግ ሀገራችን ኢትዮጵያ 

በግብርናውዘርፍ የጀመረችውን የምርታማ እና የማንሰራራት ዘመን ወደ ከፍታ 

ማማ ማድረስይጠበቃል ተብለዋል።

የብሔራዊ አንድነትን፣ሀገራዊ ምክክርና መግባባት ማጠናከር የጋራ ዕሴቶች ላይ 

የተመሠረተየጋራ አስተሳሰብ በማጠናከር የወል ትርክትን በማሳደግ ጠንካራ ሀገር 

ለመገንባትቁልፍ ሚና እናዳለው ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ለሀገራዊ መግባባት መላው የክልላችን ህዝቦች 

የዜግነትድርሻቸውን በላቀ ደረጃ እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Image