የክልሉ መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት እና የመልካም
አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ ነው:-ርዕሰ መስተዳድር
የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 6/2019፦"በመደመር መንግስት የህዝብ ድምጽ
የጋራተሳትፎ የጋራ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ
ህዝባዊየምክክር መድረክ ተካሂዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት
(ዶ/ር)ከሀዲያ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በነበራቸው
የውይይትመድረክ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን
የልማትእናየመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ ነው
ብለዋል።
የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል ያለንን ሀብት፣ጊዜ እና ጉልበት አቀናጅቶ
መጠቀምእንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሌብነትን በፍጹም አንታገስም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የመላው
ህዝብድጋፍ እንደሚያሻም ጠቅሰዋል።
ያለንን የተፈጥሮ ጸጋ ማልማት ባለመቻላችን ከድህነት ጋር እየኖርን ነው
ብለዋል።
ህዝቡ በትምህርት፣በጤና፣በመንገድ እና በሌሎችም መስኮች መሰረታዊ
ጉዳይመሆኑን አብራርተዋል።
እርስ በርስ የመከባበር እሴቶቻችን የጋራ ሀብቶቻችን ናቸው ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩይህን ለልማት መጠቀም ተገቢ ስለመሆኑም አጽንኦት
ሰጥተዋል።
አቅሞቻችንን ሰብስበን እና ጸጋዎቻችንን ጥቅም ላይ በማዋል የህዝብን
ህይወትመቀየር አብይ አጀንዳችን ነው ብለዋል።
የገነባነውን ሰላም ብሎም የመሰረተ ልማቶችን አለመጠበቅ ለችግሮቻችን
መነሻነውሲሉም ጠቅሰዋል።
አመራሩ የመደመር መንግስት ባህሪያትን መላበስ አለበት ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጽናት ባህል እና ቋንቋችንን
ለጋራእድገት መጠቀም ተገቢ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
በምንሰራው ስራ ሁሉ የዜጎችን ክብር ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩበፈጠራ፣በፍጥነት በጥራት እንዲሁም በስፋት ማምረት
የመደመርመንግስት መገለጫዎች መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ
አስታውቀዋል።
ወጣቶች ክብራቸው ተጠብቆ በአካባቢያቸው ሰርተው እንዲለወጡ ትኩረት
መስጠትእንደሚገባም ጠቅሰዋል።
የመደመር መንግስት የመጨረሻው ግብ የኢትዮጵያን ስልጣኔ መገንባት ነው
ሲሉምርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የሰለጠኑ ሀገራት ጽናት፣ችግርን መቋቋም ዘመን ተሻጋሪ ሀሳብ ሰንቀቆ መስሬረት
መገለጫቸውመሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉአላዊነቷን አስጠብቃ ትውልድ እያሻገረች ስለመሆኑም
አብራርተዋል።
ያለንበት ዘመን ትንሽ ሰርተን ብዙ የምናርፍበት ሳይሆን ጉልበት፣ገንዘብ እና
እውቀትንበመጠቀም ሳንታክት የምንሰራበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።