የመደመር መንግስት ስንፍናን እና ልግመኝነትን አይታገስም :-
ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 7/2019 "በመደመር መንግስት ህብረተሰብ
አቀፍ የምክክር መድረክ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ተካሂዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት
(ዶ/ር) በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት የመደመር
መንግስት ስንፍናን እና ልግመኝነትን አይታገስም ብለዋል።
የህዝቡን ፍላጎት ማዳመጥ፣የህዝቡን ችግር መፍታት፣ብልሹ
አሰራር እና ሌብነትን አጥብቀን እንታገላለን ሲሉም ጠቅሰዋል።
አገልግሎትን በገንዘብ መግዛት ወንጀል ስለመሆኑም ርዕሰ
መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የመደመር መንግስት የክልላችንን ጸጋዎች በመለየት ማልማት ተገቢ
ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ በተትረፈረፈ ሀብት ላይ ያለች ነገር ግን ያላትን ሀብት
ያልተጠቀመች ሀገር መሆኗን አስረድተዋል።
ጸጋዎቻችንን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ በትኩረት
እንሰራለን ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የስልጤ ህዝብ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በሰላም እና በትብብር ለመስራት
ላሳየው ተሳትፎ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ መንግስት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ላይ አብይ አጀንዳ በማድረግ
እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በእይታም በባህሪም የተለየ መንግስት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
የኢትዮጵያን ስልጣኔ መገንባት የሚያስችል አቅም መፍጠሩን ርዕሰ
መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ስልጣኔን የገነባ ሀገር በጠንካራ መሰረት ላይ ይገኛል ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩ ለመጪው ትውልድ የገነባነውን ሀገር ማስቀጠል ተገቢ
መሆኑንም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የባህር በር
የማግኘት ፍላጎት እናሳካለን ብለዋል።
እንደ ሀገር በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ አልቀን አስበን እየሰራን
ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
የሰው ሀይል፣የገንዘብ እና የተቋም አቅማችንን በማደራጀት ወደሚፈለገው
የእድገት ደረጃ እንሸጋገራለን ብለዋል።
ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን
ለመፍታት የትብብር እና የመደጋገፍ ባህል ማሳደግ እንደሚገባም
ጠቅሰዋል።
የመደመር መንግስት ሰው ተኮር፣ዜጋ ተኮር፣የዜጎችን ክብር ማረጋገጥ
መገለጫዎች ስለመሆናቸውም አመላክተዋል።
ግንባታቸው የተጓተቱ የልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ የመደመር
መንግስት ባህሪ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በስፋት በማምረት
የህዝብተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኩራል ብለዋል።
ስራፈጣሪነት ሌላኛው የመንግስት አቅጫጫ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ
መስተዳድሩከግሉ ሴክተር ጋር በትብብር እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ከፍ የምትልበት ዘመን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በአህጉር
ደረጃ ድምጿን ማሰማት የምትቾልበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።