Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ 

ልዩልዩ የልማት ስራዎች ምልከታ እያደረጉ ነው 

ሆሳዕና ፣ጥቅምት 7/2019 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ 

ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ምልከታ እያደረጉ ነው 

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልኡክ የወራቤ ኢንዱስትሪ መንደር 

ምልከታ አካሂዷል። 

በኢንዱስትሪ መንደሩ 202 ባለሀብቶች እያለሙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 

46 ፕሮጀክቶች ግንባታቸውን ስለማጠናቀቃቸው ተመላክቷል።

4 ፋብሪካዎች ደግሞ ወደ ስራ መግባታቸውም ተጠቁሟል። 

ለየኢንዱስትሪ መንደሩ የመንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች 

ተደራሽነት ላይ እየተሰራ መሆኑም በመስክ ምልከታው ተጠቁሟል። 

60 ሄክታር መሬት መርካቶን በወራቤ በሚል እሳቤ የማዘጋጀት ስራ 

ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል።

ወደ 84 ሄ/ር የሚጠጋመሬት ለደረቅ ወደብ ዝግጁ መደረጉም በዚሁ 

ጊዜ ተመላክቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የወራቤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣የወራቤ 

ወንዝዳርቻ ልማት እንዲሁም በከተማው በግንባታ ላይ የሚገኘውን 

የኮሪደር ልማት ተመልክተዋል።

Image