Skip to main content

በሁሉም መስክ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር 

ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት በልዩ ትኩረት 

ይሰራል :-ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ጥቅምት 8/2019፦"በመደመር መንግስት ህብረተሰብ አቀፍ የምክክር

መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በውይይት 

መድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት በሁሉም መስክ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት 

እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት 

በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። 

የህዝብን ድምጽ ማድመጥ እና ለችግሮች መፍትሄ መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀዉ 

የአመራር ጥበብ ነው ብለዋል። 

የመደመር መንግስት የህዝቡን ህይወት ለመቀየር ያለውን ቁርጠኝነት ርዕሰ 

መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

ጉራጌ የሀገር ኩራት የሆነ ማህበረሰብ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ታሪክን፣ቋንቋን 

እንዲሁም ባህልን መጠበቅ ማልማት እና ለትውልድ ማሸጋገር እንደሚገባም አጽንኦት 

ሰጥተዋል።

ያሉንን ጸጋዎች በማልማት ለኢኮኖሚያዊ፣ለሰላምና ለማህበራዊ ፍትህ አገልግሎት 

ማዋልወሳኝ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። 

የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የክልሉ መንግስት አብይ ጉዳዮች መሆናቸውንም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ክልላዊ አቅም መገንባት ይኖርብናል ብለዋል። 

የምንፈጥረውን ሰላምና ደህንነት በጽኑ መሰረት ለመገንባት ከሀገር ሽማግሌዎች እና 

ከሀይማኖት አባቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የዜጎችን ክብር ማረጋገጥ፣ፈጠራ፣ፍጥነት እና ጥራት ፣

የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማጠናቀቅ የመደመር መንግስት መገለጫዎች 

መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

የመደመር መንግስት በስፋት የሚያመርት፣ስራ ፈጣሪ፣ከህዝብ፣መንግስታዊ ካልሆኑ 

ተቋማት እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር የሚሰራ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ 

ጠቁመዋል።

በሁሉም ዘርፍ ተግባራዊ በሚደረጉ ስራዎች የዜጎች ችግር መፍታት የሚያስችሉ 

ስለመሆኑ ማረጋገጥ የመደመር ባህሪ መሆኑን ጠቁመዋል።

Image