የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ያለመታከት በልዩ ትኩረት
እንሰራለን :- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 11/2019፦"በመደመር መንግስት ህብረተሰብ
አቀፍ የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት
(ዶ/ር) በምክክር መድረኩ እንዳሉት ጉራጌ በጠንካራ ማህበራዊ
የትስስር እሴቶች እና በራስ አገዝ የልማት ስራዎች አርአያነት ያለው
ተግባር ሲያከናዉን ቆይቷል ብለዋል።
ይህን ተከትሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰው አክባሪነት፣በስራ ፈጣሪነት
፣በስራ ወዳድነት እና በታታሪነት የሚጠቀስ ታላቅ ህዝብ ስለመሆኑም
ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ አለመግባባትን በዲሞክራሲያዊ እና በሰለጠነ መንገድ
የሚፈታበ ትዘመን ተሻጋሪ የባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ያለው መሆኑን
ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በህዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላትን ሴራ የሀገር ሽማግሌዎች
፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶች እና ሴቶች በማስተዋል እና በጥበብ ማክሸፍ
እንዳለባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
መንግስት የሀገርን ትልቅነት፣የዜጋን ክብር የሚያሳድጉ ከፍ ከፍ ያሉ ውጥኖች
እንዳሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር የመደመር ስትራቴጂ መቀረጹ ዘመን ተሻጋሪ የብልጽግና መሰረት
መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ከፊታችን አድካሚ ስራና ረጅም መንገድ አለ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የማደግ
እና የመበልጸግ ተስፋችን በግልጽ ራዕይ እና ስትራቴጂ እየተመራ ስለመሆኑም
ጠቅሰዋል።
የምናባክነው ጊዜና ጉልበት የለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሮቻችንን በምክክር
እና በውይይት በመፍታት በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ዘላቂ ሰላም ማስፈን
አብይ ጉዳያችን ነው ብለዋል።
የህዝባችንን የተሟላ ዘላቂ ሰላም ለመመለስ ቀንና ማታ ሳንል ያለመታከት እንሰራለን
ብለዋል።