Skip to main content
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ፣
ሆሳዕና፣ጥር 14፣ 2017 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከዚህ ቀደም በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ ቀበሌያት በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት የክልሉ መንግስት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
በግጭቱ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘላቂና ጊዜያዊ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የጀመረዉን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል ።
ከግጭቱ ማትረፍ የፈለጉ ሀይሎች የቀጠናውን ሰላም እንዳይረጋጋ ያደረጉት ጥረት በሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ፣በሀገር ባህል ሽማግሌዎች፣በሀይማኖት አባቶች፣በአመራሩ እና በጸጥታ ሀይሉ የላቀ ጥረት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት።
በሁለቱም ወገኖች ተፈናቅለው አሁን ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው የላቀ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
#ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን
Image
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ፣