Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በጠምባሮ ልዩ ወራዳ 

የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ 

(ሆሳዕና ፣ጥቅምት 14/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ልዩ ልዩ 

የልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል። 

በልዩ ወረዳ ከህዝባዊ የምክክር መድረክ በተጓዳኝ በመንግስት እና 

በግል ባለሀብቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ስራዎችን ተመልክተዋል። 

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ ዱርጊ -ኦሞ ወንዝ -26 ነጥብ 

7 ኪ/ሜ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተመልክተዋል። 

በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳድሩ በልዩ ወረዳው በነበራቸው ቆይታ 

41ኪ/ሜ የሚሸፍነውን የወልደ ሀኒ ዱርጊ አስፋልት መንገድ ግንባታ 

ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ 

ካላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በፍጥነት መጠናቀቅ 

እንዳለባቸው አሳስበዋል። 

የመንገድ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር 

በማጠናከር የተጀመረውን የእድገት ጉዞ ለማፋጠና ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው 

የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠት ተገቢ ስለመሆኑም 

አመላክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሁለቱም ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ተግዳሮት በሆኑ 

ጉዳዮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

የወልደ ሀኒ ዱርጊ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከ2 ነጥብ8 ቢሊየን በላይ ብር 

ወጪ እንደሚደረግበት ተመላክቷል። 

የመንገድ ፕሮጀክቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ከኦሮሚያ እና ከደቡብ 

ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር ያገናኛል።

 

Image