መላው አመራር የህዝብን ችግር በመረዳት ተነሳሽነት ወስዶ በላቀ
ቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል:- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ
አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 15/2019' በመደመር መንግስት ህብረተሰብ አቀፍ
የምክክር መድረክ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተከሂዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት የሀላባ ህዝብ የትብብር እና
የአንድነት ማሳያ ነው ብለዋል።
ተነሳሽነት እና የጋራ ግብ የመደመር መሰረታውያን መሆናቸውን የገለጹት
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ተከትሎም የሀላባ ህዝብ በቃል ሳይሆን በተግባር
አሳይቷል ብለዋል።
መላው አመራር የህዝብን ችግር በመረዳት ተነሳሽነት ወስዶ መስራት እንዳለበትም
ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
ድህነትን ለማሸነፍ ቀዳሚው ጉዳይ ለጋራ ግብ መስራት ስለመሆኑም ርዕሰ
መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
መድረኩ የህዝቡን ችግር በማዳመጥ በትብብር መስራት የሚያስችል አቅም
መፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
የክልሉ መንግስት በየደረጃው ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት
ያለውን ቁርጠኝነት ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
መንገድ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር በመፍታት ረገድ
ካለውየላቀ አበርክቶ አንጻር በዘርፉ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት
እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በመብራት፣በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣በሰላምና ጸጥታ፣በጤና፣በትምህርት፣
በቴሌኮም፣በመብራት እና በሌሎችም የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ላይ ለተነሱ
ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራም አብራርተዋል።
የክልሉ መንግስት አብይ ዓላማ በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ለዘላቂ ሰላም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጹት ርዕሰ
መስተዳድሩ ህግና ስርዓት ማስከበር ተገቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
በሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ እና የጸና ሰላም ለማረጋገጥ የሀገር ሽማግሌዎች እና
የሀይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
የመደመር መንግስት የኢኮኖሚ ብልጽግና የሚረጋገጠው ጸጋዎቻችንን በመለየት
እና በማልማት እንዲሁም አቅሞችን አሰባስቦና አቀናጅቶ ለውጤት በማብቃት
መሆኑን ያምናል ብለዋል።
የመደመር መንግስት በስፋት የሚያመርት፣ስራ ፈጣሪ፣ከህዝብ፣መንግስታዊ ካልሆኑ
ተቋማት እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር የሚሰራ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ
ጠቁመዋል።