admin
Tue, 01/28/2025 - 16:27
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ
ሆሳዕና፣ ጥር 15፣ 2017፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ ይገኛል ።
መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉን መንግስት በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ በስፋት እንደሚመክር ተመላክቷል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት ልዩ ልዩ የኢንቬስትመንት ጥያቄ ፕሮጀክቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።
መስተዳድር ምክርቤቱ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎች ውስጥ በክልሉ በሰባት ማዕከላት የቢሮ ግንባታ ስራ ማስጀመርን ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍም ተመላክቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ እንደገለጹት መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከድህነት መውጣት በሚቻልባቸው አብይ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው እንዳመላከቱት በግብርና፣በኢንዱስትሪ ፣በማኑፋክቸሪንግ ፣በቱሪዝም፣በማዕድን እና በቴክኖሎጂ /ዲጂታላይዜሽን ዘርፎች ከድህነት ለመውጣት አብይ ጉዳዮች ስለመሆናቸው ጠቁመዋል።
በሌሎች ዘርፎች የሚካሄዱ ስራዎች ከላይ የተጠቀሱትን የትኩረት መስኮች የሚያሳኩ ሊሆን እንደሚችል ታሳቢ ማድረግ ይገባል ብለዋል
የክልሉ መንግስት እቅድ ላይ አስቀድሞ የጋራ መግባባት በመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በመፈተሽ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በጤናው ዘርፍ በወባ በሽታ መከላከል ላይ በልዩ ተትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በሌሎችም ሴክተሮች የታቀዱ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት የታቀዱ ተግባራት አፈጻጸም ላይ የተመዘገቡ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ መስተዳድር ምክር ቤቱ በዝርዝር እንደሚወያይ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
Image
