admin
Tue, 01/28/2025 - 16:44
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተወከሉ የሀገር/ የባህል ሽማግሌዎች ጋር አብሮነትን በማፅናት ፣ ሠላምን በማስፈንና ልማትን በማፋጠን ዙሪ ምክክር እያካሔዱ ነው ፤
ሆሳዕና፣ጥር 18፣ 2017 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተወአሉ የሀገር/ የባህል ሽማግሌዎች ጋር አብሮነትን በማፅናት ፣ ሠላምን በማስፈንና ልማትን በማፋጠን ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ምክክር እያካሔዱ ይገኛል ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባባቸው ጊዜያት ወዲህ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በተመለከተ ለሀገር ሽማግሌዎቹ አጭር ገለጻ አድርገውላቸዋል።
የክልሉን የመልማት አቅም እና ጸጋዎች ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የባህል/የሀገር ሽማግሌዎች መድረኩ የክልሉን ሕዝቦች ዘመን ተሻጋሪ የጋራ እሴቶችን መሠረት በማድረግ የህዝቦችን ትስስርና አብሮነት ለማፅናት፣ ዘላቂ ሠላምን እዉን ለማድረግ የህዝቦችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሻሻል አጋዥ መሆኑ ተጠቁሟል።
Image
