Skip to main content
ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተመሰረተ፤
ሆሳዕና፣ ጥር 18፣ 2017 ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተመሰርቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር የሽማግሌዎች ፎረም ሰብሳቢ ዳኛ ሞላ ጫኬቦ እንደገለጹት ፎረሙ እንዲመሰረት ለክልሉ መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።
የፎረሙ መመስረት አብይ ዓላማ የክልሉን ህዝቦች የእርስ በርስ መስተጋብር ከማጠናከሩም በላይ ከመንግስት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢው ጠቁመዋል።
ፎረሙ የክልሉን ህዝቦች አንድነት ለማስጠበቅ፣ቱባ ባህሎችና እሴቶች ለማጎልበትና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሰብሳቢው አመላክተዋል።
የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም አባላት በክልሉ የሚነሱ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር ለማስፈጸም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
የፎረሙ አባላት ሁሉንም የክልሉን ህዝቦች በእኩልነት በፍትሀዊነት እና በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውንም በቃለ መሐላ አረጋግጠዋል።
የሽማግሌዎቹ ፎረም የክልሉ መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥና ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ለማገዝ መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።
ፎረሙ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ሲመሰረት የተለያዩ የስራ አስፈጻሚዎችን በመምረጥ ወደስራ ገብቷል።
Image
ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተመሰረተ፤