admin
Tue, 02/11/2025 - 12:22
የጉባኤው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ከድህነት የመውጫ መሳሪያዎች እና የሀገር ግንባታን የምናረጋግጥባቸዉ ናቸዉ - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
"መፍጠን እና መፍጠር ፣ለጉባኤያችን ውሳኔዎች ስኬት " በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የአመራር የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በምክክር መድረኩ እንደገለጹት የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ከድህነት የመውጫ መሳሪያዎች እና የሀገር ግንባታን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል።
በጉባኤው የለውጡ የ6 ዓመታት ስኬቶች እና ቀሪ ስራዎች ተለይተው ሰፊ ውይይት ተካሔዶባቸዋል ብለዋል።
የአንደኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎችና አፈጻጸሞች ያሉበትን ደረጃ መለየት ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከጉባኤው አቅጣጫ ውሳኔዎች በላይ የተፈጸሙ ተግባራት እንደነበሩም የጋራ መግባባት ስለመፈጠሩ ጠቁመዋል።
ከአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ስለ ጉባኤው ስኬታማነት የደስታ መግለጫ ማስተላለፋቸው የብልጽግና ጉዟችን ወደ ሌሎች ሀገራት መሸጋገሩን አመላካች ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የፖለቲካ ስራውን የሚመሩ እና የሚያስተባብሩ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና የምክር ቤት አባላት ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መምረጥ የተቻለበት ጉባኤ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።
የጉባኤው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች በየደረጃው ላሉ ለአመራሮች፣ለመንግስት ሰራተኞች እና ለህዝቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተግባራዊ እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እንደገለጹት የጉባኤው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች የመላውን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።
የብሔራዊነት ገዢ ትርክት፣የወል ትርክት እንዲሁም የአብሮነት ትርክት ከሚኖራቸው የላቀ ፋይዳ አንጻር የውሳኔው አቅጣጫዎች ናቸው ያሉት ኃላፊው የሀገር ግንባታን ማጠናከር
እንዲሁም ማህበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ማተኮር እንደሚገባም መመላከቱን ጠቁመዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙን ማጠናከር እንዲሁም የህዝብን ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚያስችሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራትን በተሻለ ደረጃ መፈጸም የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡንም ዶ/ር ዲላሞ አስረድተዋል።
ጉባኤው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ትልቅ ትርጉም የነበረው ነው ያሉት ኃላፊው ሀገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያመላከተ እንደነበር ተናግረዋል።
በመጀመሪያው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች ላይ በስፋት መምከር ተችሏል ያሉት ኃላፊው በተለይ የፖለቲካ ምህዳርን ከማስፋት አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም ስለመቻሉም አብራርተዋል።
በሀገሪቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን አንጻር የተከናወኑ ስራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ያስቻለ ጉባኤ እንደነበርም ዶ/ር ዲላሞ አስታውሰዋል።
ከኢኮኖሚ አንጻር በሌማት ትሩፋት፣በመስኖ፣በአረንጓዴ አሻራ፣በማኑፋክቸሪንግ ኢንዳስትሪ፣በአገልግሎት እና በሌሎችም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ላይ የተከናወኑ ተግባራት እና ያጋጠሙ ችግሮችን መፈተሽ እንደተቻለም ጠቁመዋል።
ከ #ከክልሉ መንግሰት ኮሙኒኬሽን
Image
