admin
Sat, 03/29/2025 - 09:10
ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ፊቼ ጫምበላላ’ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
ለመላዉ የሲዳማ ህዝብ ፣ እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ፊቼ ጫምበላላ’ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! እያልኩ የመልካም ምኞት መልዕክቴን አስተላልፈዋል ፤
'ፊቼ ጫምበላላ’ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የኢትዮጵያን ብዝሃ ማንነት ከሚመሰክሩ አብነቶች አንዱ ነዉ፤ ማንነትና ኢትዮጵያዊ አንድነት ፣ በሕብረ _ ብሔራዊ የብዝሃነት ማዕቀፍ ተደጋግፈዉና ሚዛናቸዉን ጠብቀዉ ሲራመዱ፣ በጋራ እሴቶች የተመሠረተ የወል ትርክት ለመንገባት እና ጠንካራ ሀገረ መንግስትና ብሔረ መንግስት ለመገንባት መደላድል ይፈጥራሉ።
ፊቼ ጫምባላላ የወንድም/እህትማማችነት እሴቶችን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ለማሸጋገር ከሚያግዙ ባህላዊ ገፀ በረከቶች አንዱ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ፤ የእርቅ፣ የሰላምና የአብሮነት ማጠናከሪያ ባህላዊ እሴትም ነዉ።
በዓሉ የህዝቦችን ዘላቂ ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን ለማድረግ አዲስ መነሳሳት የምንጎናፀፍበት እንዲሆን እመኛለሁ፣
መልካም በዓል!
Image
