admin
Thu, 05/01/2025 - 19:49
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በአቶ አሊ ከድር ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ
(ሆሳዕና፣ሚያዚያ 20/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ አሊ ከድር ባጋጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
አቶ አሊ ከድር በወረዳ ፣በዞን እና በክልል ተቋማት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ስራቸውን በብቃት እና በታማኝነት ሲወጡ እንደነበርም ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው አመላክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው ለቤተሰባቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
Image
