Skip to main content

ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ፊቼ ጫምበላላ’ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! ለመላዉ የሲዳማ ህዝብ ፣ እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ፊቼ ጫምበላላ’ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! እያልኩ የመልካም ምኞት መልዕክቴን አስተላልፈዋል ፤ 'ፊቼ ጫምበላላ’ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የኢትዮጵያን ብዝሃ ማንነት ከሚመሰክሩ አብነቶች አንዱ ነዉ፤ ማንነትና ኢትዮጵያዊ አንድነት ፣ በሕብረ _ ብሔራዊ የብዝሃነት ማዕቀፍ ተደጋግፈዉና ሚዛናቸዉን ጠብቀዉ ሲራመዱ፣ በጋራ እሴቶች የተመሠረተ የወል ትርክት ለመንገባት እና ጠንካራ ሀገረ መንግስትና ብሔረ መንግስት ለመገንባት መደላድል ይፈጥራሉ። ፊቼ ጫምባላላ የወንድም/እህትማማችነት እሴቶችን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ለማሸጋገር ከሚያግዙ ባህላዊ ገፀ በረከቶች አንዱ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ፤ የእርቅ፣ የሰላምና የአብሮነት ማጠናከሪያ ባህላዊ እሴትም ነዉ። በዓሉ የህዝቦችን ዘላቂ ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን ለማድረግ አዲስ መነሳሳት የምንጎናፀፍበት እንዲሆን እመኛለሁ፣ መልካም በዓል!

Image
ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ፊቼ ጫምበላላ’ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!