admin11
Mon, 09/01/2025 - 12:22
Image

Title
የቱሪዝም ዘርፉ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዋልታ በመሆኑ ቱሪዝምን ለማጠናከር
ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ማስፋፋት ይገባል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ወጪ የማስፋፊያ ግንባታ የተደረገለት
የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል መርቀው ከፍተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሆቴሉ ምረቃ ወቅት እንደገለፁት ፣በቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ
እድገት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ዘርፎች አንዱ በመሆኑ ለዚሁ ዘርፍ
አጋዥ የሚሆኑት ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ማስፋፋ ይገባል ።
በወልቂጤ ከተማ የማስፋፊያ ግንባታዉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት የበቃው የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል
ለሌሎች ባለሀብቶች መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለሆቴሉ ባለቤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።