የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ብልጽግና ማረጋገጥ አብይ አጀንዳዎቻችን ናቸው :-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ግንቦት 13/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ
መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ
የባለ ብዙ መንደር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን
ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
እንደገለጹት የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ብልጽግና ማረጋገጥ የመንግስት
እና የብልጽግና ፓርቲ አብይ አጀንዳዎች ናቸው ብለዋል።
ውሃ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ጠቀሜታ ዘርፈ ብዙ ነው ሲሉም
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ
አካላት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።
ብልጽግና ፓርቲ እና መንግስት በተለያየ ጊዜ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን
በማጠናቀቅ የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው
ስራ ተግባራዊ እያደረጉ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የተመረቁ ፕሮጀክቶችን ህዝቡ በአግባቡ እንዲጠብቅ እና እንዲያስተዳድር
ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
የሳንኩራ ወረዳ ህዝብ ከመላው አመራር ጋር በመሆን በክልሉ ተግባራዊ በሚደረጉ
የልማት ስራዎች ላይ ተጨማሪ አቅም እየፈጠሩ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ
አስረድተዋል።
የወረዳው ህዝብ እና አመራሩ በሰላም ፣በገቢ ፣በትምህርት፣ ጤና፣በንግድ፣
እና በኢንቬስትመንት ዘርፎች የላቀ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ብልጽግና ማረጋገጥ አብይ
አጀንዳዎቻችን ናቸው :- ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)