admin11
Wed, 06/03/2026 - 10:48
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ
ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ
Image
Title
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወራ ቤከተማ
ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ
ሆሳዕና፣ግንቦት 26/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት
የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ
የወራቤ ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከል
በ15 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተመላክቷል።
የግብይት ማዕከሉ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን
አምራቹን እና ሸማቹን ማህበረሰብበ ቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን
በማረጋጋት ረገድ የጎላ ሚና እንዳለውም ተጠቁሟል።
በማዕከሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ቀርቦ ግብይት እየተካሔደበት ነው።