admin11
Wed, 06/03/2026 - 11:00
የተከበራችሁ መላው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች፣
የየደረጃው አመራሮች ፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች፣
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ በአጠቃላይ መላው የሕብረተሰብ ክፍሎች፣
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ በእናንት ኃላፊነት በተሞላበት ንቁ የዜግነት ተሳትፎ፣
ሀገርን የማስቀደምና የማስቀጠል ፅናትና የአስተዋይነት መንፈስ ታጅቦ
በሠላማዊና በሠከነ ሁኔታ ተጠናቅቋል ፤ኢትዮጵያ መርጣለች!
የሀገራችን_ ኢትዮጵያ፣ተስፋዋ እንዲለመልም፣፣ልዕልናዋ እንዲፀና፣መፃኢ ዕጣፈንታዋ
ብሩህ እንዲሆን አኩሪ አስተዋጽኦ አበርክታችኋል፤
ብርድ ፣ፀሐይና ዝናቡንም ተቋቁማችሁ፣ታሪክ ሠርታችኋል ፣ ለዴሞክራሲ
ግንባታው ሂደት ማበብ ጉልህ ዐሻራ አኑራችሁዋል፤
ለዚህከፍተኛ አስተዋጽኦ፣በክልሉ መንግስት እና በእራሴስም፣
ምስጋናዬን በታላቅ አክብሮት አቀርባለሁ።
በሕዝቦች ንቁ ተሳትፎና ዐሻራ የጀመርነዉ የዴሞክራሲ፣የሠላም እና የልማት ግንባታ
ወደ አዲስ ምዕራፍ ይሸጋገር ዘንድ መላው ሕዝባችን የጀመረዉ ንጥረት አጠናክሮ
እንዲቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ!
አመሠግናለሁ!
Image