ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን
ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ነው :- ርዕ ሰመስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር
ሆሳዕና፣ሰኔ 11/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካውንስል
የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሬሽንና የቀዳማይ የልጅነት
ፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
እንደገለጹት የምግብ ስርዓት ሽግግርና ፍኖተ ካርታ አብይ ዓላማ ያደገና
ዘላቂ የምግብ ስርዓት መፍጠር ነው ብለዋል።
ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ስራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያመላከቱት
ርዕሰ መስተዳድሩ የግብርናው ዘርፍ ሲሻሻል የምናልማቸውን ግቦች ማሳደግ
እንደሚያስችልም አስረድተዋል።
ህጻናት በልጅነታቸው በሚመገቡት ፣ በሚያዩት ፣በሚሰሙት እና በሚዳስሱት
ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ ያድርባቸዋል ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ ጤናማና ንቁ ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን ላይ
በትኩረት መስራት ተገቢ ስለ መሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በትውልድ ግንባታ ላይ መስራት ለሀገር ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ
ከፍተኛ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።