በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን ይሁንታ ወደ
ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ሰኔ 16/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓም
የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን ይሁንታ ወደ
ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል ብለዋል።
በጎነት የመስጠት እና የማካፈል መርህ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
በተለይ ተማሪዎችን ማስተማር፣በስነ ምግባር እንዲታነጹ በማድረግ
ለቀጣዩ አመት ዝግጁ እንዲሆኑ መደገፍ ይገባል።
ከእውቀት ሽግግር ባለፈ ሀብትን እና ጊዜን በማካፈል የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ስራ ማከናወን ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም
የሁሉንም አካላት ተሳትፎ እና ትብብር ይጠይቃል ብለዋል።
የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ እሴትን በማጎልበት የሰዎችን ስሜት መረዳት
የበጎነት መገለጫ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የድህነትን ቅነሳ አንዱ አካል ነው ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ መተባበርን እና አብሮነትን የምናጸናበትን እድል
የሚፈጥር ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።
በመረዳዳት ውስጥ የጋራ ትርክትን የምንፈጥርበት ነው ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን
ይሁንታ ወደ ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል ብለዋል።