በሁሉም ዘርፍ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት እንዲኖረው መስራት ይገባል:-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ሰኔ 16/ 2018 :- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓም
የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ
በይፋ ተጀምሯል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
የአንዲትን አረጋዊት ቤት ግንባታ ባስጀመሩበት ጊዜ እንደገለጹት
በክልሉ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የአንድ ወቅት ብቻ ሊሆን አይገባም ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ ስራው ዘላቂነት እንዲኖረው ማተኮር ተገቢ ስለመሆኑም
አጽንኦት ሰጥተዋል።
አረጋውያንን መርዳት፣የአካባቢ ችግርን መፍታት ካለን እያካፈልን የዜጎችን
ተጠቃሚነት ማሳደግ የህሊና እርካታ እንደሚሰጥ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በክልሉ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1ሺ በላይ ቤቶች እንደሚገነቡ የገለጹት
ርዕሰ መስተዳድሩ የቤቶች ደረጃ ዲዛይን መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
በዘርፉ የሚካሔደውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬታማ ለማድረግ መላው ህዝብ፣
አመራሩ እና ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።