admin11
Tue, 07/14/2026 - 18:45
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የሆሳዕና ከተማ
የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ምልከታ አደረጉ
ሆሳዕና፣ሐምሌ 6/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሆሳዕና ከተማ
ከ588 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን
የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል
የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማውን
ሳኒቴሽን በእጥፍ እንደሚያሳድገው ተመላክቷል።
ለ1ነጥብ 5 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት
የሚሰጠው ይህ ፕሮጀክት በቀን 250 ሜትር ኪውብ ውሃ
በማጣራት ለመስኖ አገልግሎት እንዲውል የላቀ አስተዋጽኦ
ያበረክታል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የሆሳዕና ከተማ
የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ ሚያዚያ 29/2017 የመሰረት
ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
Image