Skip to main content
በትምህርት ዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ የላቀ ድጋፍ እና ትብብር ይፈልጋል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በትምህርት ዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ የላቀ ድጋፍ እና ትብብር ይፈልጋል:-

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)


ሆሳዕና፣ነሐሴ 29/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው የትምህርት 

ሴክተር ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው 

እንደገለጹት የትምህርት ስራ የላቀ ትብብር ይፈልጋል ብለዋል። 

የትምህርት ስራ ተዋናዩ እና ባለድርሻ አካላት በርካታ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ልዩ ትኩረት ያሻል በማለት ገልጸዋል። 

በማደግ ላይ ያሉ እና ያደጉ ሀገሮች ሀገራቸውን የለወጡት በትምህርት ነው ብለዋል። 

በትምህርት ላይ ያላቸው አቋም ጠንካራ ስለነበረ ትምህርትን ተጠቅመው ሀገራቸውን 

ገንብተዋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ፊላንድ፣ኖርዌይ፣ሲውዲን እና ሌሎች ሀገራት በትምህርት ላይ መስራት የጀመሩት 

ከዛሬ 50 ዓመታት ገደማ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል። 

እንደ ቻይና የመሳሰሉት ሀገሮች የትምህርት ስርዓታቸውን ገምግመው መስራት 

የጀመሩት የዛሬ 40 ዓመታት አካባቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

እነዚህ ሀገራት በትምህርት ላይ በሰሩት መጠን ሀገራቸውን መለወጥ መቻላቸውን 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

ትምህርት የህዝብንም የመንግስትንም ትኩረት እንደሚያሻ ርዕሰ መስተዳድሩ 

በንግግራቸው አብራርተዋል። 

የአንድን ሀገር ስርዓት ለማቃናትም ሆነ ለማፍረስ ትምህርት ከፍተኛ ሚና እንዳለው 

ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

ትምህርት ከተጠቀምንበት ሀገራትን ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ በቀላሉ እንዲሸጋገሩ 

ያስችላል ብለዋል። 

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርትታሪክ የ110 ዓመታት እድሜ እንዳለው ርዕሰ መስተዳድሩ 

ጠቁመዋል። 

በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ችግሮች መንስኤ የትምህርት ውጤት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

አለመከባበር እና የግብረ ገብነት ችግር ከዚህ ይመነጫል ሲሉም ጠቅሰዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 3ኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ አስመልክቶ የተዘጋጀ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው ለእይታ ክፍት አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 3ኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ 

አስመልክቶ የተዘጋጀ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና የፎቶ አውደ ርዕይ 

መርቀው ለእይታ ክፍት አደረጉ 

ዘላቂ የትምህርት ጥራት ለላቀ የመማር ውጤት እና ብልጽግና በሚል መሪ 

ሀሳብ 3ኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። 

በኤግዚቢሽኑ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ቀርበው ለእይታ ክፍት የተደረጉ ሲሆን 

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት አመት ያከናወናቸውን ስራዎች የሚያስቃኝ 

የፎቶ አውደ ርዕይ ቀርቧል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ 

ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት 

በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አደረጉ

ሆሳዕና ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን 

ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ 

ሁኔታዎች ላይ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።


ካምፓኒዉ በተለይም በሴራሚክስ ማምረት ስራ ያካበተዉን ልምድ 

መነሻ በማድረግ በክልሉ ለሴራሚክስ ኢንዳስትሪ በሚሆኑ ግበዓቶች 

ዙሪያ የካምፓኒው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሊ ሺሚንግ ከክቡር 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በዝርዝር ተወያይተዋል።

ካምፓኒዉ በክልሉ የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቬስትመንትን ለማበረታታትና 

ለመሳብ በተቋቋመዉ የላይዘን መስሪያ ቤት አማካኝነት ቀደም ሲል 

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ የመስክ ምልከታ በማድረግ 

ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉን ማረጋገጡ ተመልክቷል።

Read more
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ 

አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት 

ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 21/2018 ፦ ወጣቶቹ በክልሉ በነበራቸው ቆይታ 

ግንባታቸው በስድስት ወራት ብቻ የተጠናቀቁ የልማት 

ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል። 

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት 

ወጣቶቹ ከተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ 

አገልግሎት ልኡካን ቡድን በክልሉ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 

እያከናወነ ይገኛል።

Read more
የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል ዘመናትን የተሻገረ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል ዘመናትን የተሻገረ ነው :-

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 27/2018፦ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ 

አገልግሎት ልኡካን ቡድን በጽ/ቤታቸው አቀባበል አደረጉ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት 

የረጅም ዘመናት ታሪክ አለው ብለዋል። 

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ሂደት ዘመናትን የተሻገረ ነው ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ በተለይ በአድዋ ታሪክ ወጣቶች እና ሴቶች ከፍተኛ ድርሻ 

እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል። 

ሴቶች ቀለብ ማዘጋጀት ወጣቶች ደግሞ በአርበኝነት ሀገርን የማዳን ትግል 

ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

ወጣቶች ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ በማድረግ በሀገር እድገት ላይ 

የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል። 

ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ 

ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል። 

ወጣቶች ለህዝቦች አንድነት እና ትስስር በጋራ መስራት እንዳለባቸው 

የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጉዞ 

ማጠናከር ይጠበቃል ሲሉም አብራርተዋል። 

ክልሉ በአጭር ጊዜ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በርካታ አብነታዊ 

ስራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ስራ ማስጀመር 

መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት 

በስድስት ወራት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል። 

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያደገ ስለ

መምጣቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

Read more
ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር እና ጥረት ያሻል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር እና ጥረት ያሻል:- ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
"ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ 

በሆሳዕና ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ጸጥታ 

ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው እንደገለጹት 

የሰላም ዋጋ የሚታወቀው ሰላም ሲጎድል ብቻ ነው ብለዋል። 

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር ያሻል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

የበርካታ ተዋናዮችን ተሳትፎም ይጠይቃል ሲሉም ጠቁመዋል። 

ማህበረሰቡ ቤቱን አካባቢውን፣ጎረቤቱን መጠበቅ ይኖርበታል ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የዚህ ድምር ውጤት በዘላቂ ሰላም ላይ የጎላ ሚና 

እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላከክተዋል። 

የጸጥታ ኃይሉ የማህበረሰቡን አቅም የማስተባበር፣የማቀናጀት ቀዬ፣

መንደር፣ ቀበሌዎች እና ወረዳዎች በሰላም ውለው እንዲያድሩ መትጋት 

ይኖርበታል ብለዋል። 

አንዳንድ ሀገሮች ተፈጥሮ በሚያደርስባቸው የሰላም ችግሮች ተጎጂ ሲሆኑ 

ተመልክተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ በሰው ሰራሽ 

የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጋጥመንን ችግር ለመፍታት የተቀናጀ 

ጥረት ይጠይቃል ሲሉም አስረድተዋል። 

ሚዲያዎች በሰላም ስራ ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ ከፍተኛ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ በእያንዳንዱ ሰው የእጅ መዳፍ ስር ሚዲያ አለ 

ያያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከሁሉም በላይ ትኩረቱ በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሆን 

እንደሚገባም ጠቅሰዋል። 

ለቤተሰብ ብልጽግና መረጋገጥ ሰላም የሚኖረው ድርሻ መሰረታዊ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት 

እንደሚጠይቅም አብራርተዋል። 

በየአካባቢው ለሰላም መደፍረስ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጉባኤተኛው 

በስፋት ሊመክርባቸው ይገባል ብለዋል። 

በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሰሩ እንደሚገባም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። 

ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ የማምሸት ምጣኔ እየጨመረ መጥቷል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

ህግ በማስከበር ስራ ላይ ምክር ቤቱ በዝርዝር መወያየት ይኖርበታል 

ሲሉም አብራርተዋል። 

የመንግስት ዋነኛ ሚና ህግ ማስከበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህግ 

እንዲከበር የሚፈልግ የማህበረሰብ ክፍል ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ ህግ 

እንዲከበር ፍላጎት የሌለው አካል መኖሩን ጠቁመዋል። 

ይህንን በማስታረቅ የህዝቡን ሰላም ማረጋገጥ አብይ አጀንዳ ሊሆን 

እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

ሰላም የሚጀምረው ከቤት፣ከጎረቤት፣ከአካባቢ መነሻነት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

በሀገሪቱ ወደ 4ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ልጆች በ8 ዋና ዋና አጀንዳዎች 400 

ንኡሳን አጀንዳዎች ላይ በመምከር 99በመቶ ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸውን 

በአብነት ጠቅሰዋል። 

ይህን ምክረ ሀሳብ በመንቀፍ የሚዲያ ዘመቻ የሚያካሄዱ አካላት እንደነበሩም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቁመዋል። 

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች በጽናት እና በድል አድራጊነት 

እየተሻገረች ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል

Read more
በሪፎርም እሳቤ እና በመደመር መንገድ የጀመርናቸው ስራዎች ውጤት እያስመዘገቡ ነው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በሪፎርም እሳቤ እና በመደመር መንገድ የጀመርናቸው ስራዎች ውጤት

እያስመዘገቡ ነው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 21/2018 ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት እና

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 2ኛ ዙር የጋራ የምክክር ፎረም በሆሳዕና 

ከተማ መካሄድ ጀምሯል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

የምክክር ፎረሙን በከፈቱበት ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት 

በሪፎርም እሳቤ እና በመደመር መንገድ የጀመርናቸው ስራዎች ውጤት 

እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። 

ኢትዮጵያ በአይነቱ ልዩ የሆነ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ለ46 ቀናት ከ4ሺ 

በላይ ተመካካሪዎች ከ400 በላይ ጉዳዮችን አንስተው ከ99 በመቶ በላይ 

በመግባባት በጥቂት ጉዳዮች ደግሞ የጋራ መግባባት እንዲፈጠርባቸው 

መቀመጣቸውን ጠቅሰዋል። 

በአብዛኞቹ ጉዳዮች ላይ ለመንግስት ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ የጋራ መግባባት 

በመፈጠሩ ኢትዮጵያ ተወያይታለች:- ኢትዮጵያ ተስማምታለት፣አሸንፋለች 

ብለዋል። 

ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የጀመረቻቸውን ስራዎች ለማጠናከር፣የህዝቡን 

ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያረጋገጠች ትገኛለች ብለዋል። 

በሁሉም መስክ የጀመርነው ጉዞ ትክክለኛ መሆኑን በተለያየ መንገድ ማረጋገጥ 

ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ላይ 

የተሳተፈው ህዝባችን ለጀመርነው ስራ እውቅና ሰጥቷል። 

ለወደፊትም የጀመርናቸው ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዲችሉ ህዝቡ 

ከመንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማረጋገጡን ርዕሰ መስተዳድሩ 

አስረድተዋል። 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በክልሉ በሁሉም ስራዎች ያላቸው ተሳትፎ 

ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል። 

በክልሉ በትምህርት፣በጤና፣በውሃ በተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ 

ያላቸው ተሳትፎ ጉድለትን በመሙላት ብቻ ሳይሆን ለተጀመረው የቤተሰብ 

ብልጽግና አቅም ሆነው ስለመታየታቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

የአንድ ሀገር እና ክልል እድገት የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የተገኘውን ሀብት በቁጠባ እና በተቀናጀ መልኩ መጠቀም ደግሞ 

ውጤቱን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ብለዋል። 

በታሪክ ውስጥ የተቋም እና የሀገር ግንባታ አካል መሆን ያኮራል ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የምትመች ሰላሟ የተረጋገጠ፣ዘላቂ ልማት ያላት፣

የተግባባ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። 

የሁላችንም ስነ ልቦና በሰላም እና በልማት ላይ መገንባት ይኖርበታል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ሀገሩን የሚወድ፣የሀገሩን ጥቅም የሚጠብቅ ትውልድ በመገንባት የዘመኑ አርበኛ 

መሆን ይጠበቃል ብለዋል። 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዚህ አመት በሚኖራቸው ስራዎች የተለመደውን 

ሀላፊነት በላቀ ደረጃ መወጣት እንዳለባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተዘጋጀ የፎቶ ኤግዚቢሽን መርቀው ከፈቱ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በሲቪል ማህበረሰብ

ድርጅቶች የተዘጋጀ የፎቶ ኤግዚቢሽን መርቀው ከፈቱ 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 21/2018፦ ርዕሰ መስተዳድሩ በሲቪል ማህበረሰብ 

ድርጅቶች የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የሚገልጽ የፎቶ ኤግዚቢሽን 

ስራዎችን ተመልክተዋል። 

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ስራዎችን የሚገልጽ 

የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ለህዝብ ክፍት ሆኗል።

Read more
መላው ህዝብ እና አመራር የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄ እውን ለማድረግ በሚካሄደው ጥረት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ጥሪ አቀረቡ

መላው ህዝብ እና አመራር የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄ እውን 

ለማድረግ በሚካሄደው ጥረት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ጥሪ አቀረቡ 

ሆሳዕና ፣ነሐሴ 11/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

"ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ"በሚል መሪ ሀሳብ 3ኛ ዙር 

የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ክልሉ ከተመሰረተ 

ሶስት ዓመታት አስቆጥሯል ብለዋል።በነዚህ የሶስት አመታት ጉዞ 

አዳዲስ ስኬቶችን ማስመዝገብ ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ 

በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል። 

ከነባሩ ክልል የተላለፈ እዳ ለመክፈል የተደረገው ርብርብ ውጤታማ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ግንባታቸው ተቋርጦ የነበሩ የመንገድ፣የንጹህ 

መጠጥ ውሃ፣የመስኖ፣የትምህርት እና የጤና ፕሮጀክቶች በጠንካራ 

ድጋፍና ክትትል ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን አብራርተዋል።

ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት ከ320 በላይ መለስተኛ እና መካከለኛ 

የልማት ፕሮጀክቶች በስራ ላይ መገኘታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

እነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ የክልሉን ህዝብ ተሳትፎ እና 

ተጠቃሚነት ያሳድጋሉ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

በክልሉ የህዝብ አንድነት እና ተቀራርቦ የመስራት አቅም ለማሳደግ የጋራ 

ትርክትን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እና ለቀጣይ 

ስራ መሰረት የጣሉ ስለመሆናቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

ክልሉን 24 ሰዓታት ለስራ ምቹ እንዲሆን መደረጉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በተወሰኑ አካባቢዎች ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት ተከታታይ የሰላምና ጸጥታ 

ስራ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። 

በክልሉ የ2018 በጀት ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት 10 ነጥብ 2 ማድረስ መቻሉን 

የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በግብርና 8ነጥብ 1፣ በኢንዱስትሪ 21ነጥብ 8 እንዲሁም 

በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 10 ነጥብ 5 ማድረስ መቻሉን ጠቅሰዋል። 

በከተማ እና በገጠር ነዋሪውን ህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ 

እየተካሄደ ያለው ጥረት በሁሉም መስኮች ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል። 

ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ንቅናቄ 

የብልጽግናችን አካል ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። 

የአካባቢ ብክለትን መከላከል ጤንነትን፣ምርታማነትን፣የመስራት አቅምን 

ያጎለብታል ብለዋል። 

መላው ህዝብ እና አመራር በዚህ ንቅናቄ ላይ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ 

እንዲወጣም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት 3ተኛ ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት 3ተኛ ዙር 

የፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ሆሳዕና ፣ነሐሴ 11/2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በተገኙበት 3ተኛ ዙር 

"ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መርህ የንቅናቄ መድረክ 

በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍን መሰረት ባደረገው 

ፕሮግራም ለአካባቢ መቆሸሽ እና ብክለት መንስኤ የሆኑ ችግሮችን 

በጋራ መከላከል ላይ ማተኮር ተገቢ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ሱርሞሎ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 

ፕሬዘዳንት ኤርሲኖ አቡሬ፤የኢፌዲሪ ደን አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል 

ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ጨምር የክልሉ ከፍተኛ የቢሮ ኃላፊዎችና 

ጥሪ የተደረገላች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Read more