Skip to main content
መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት የኢንቬስትመንት ልማት 

ፕሮጄክት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ሆሳዕና ፣ሰኔ 9 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት 

መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ 
በቀረቡለት የተለያዩ የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክት ጥያቄዎች 

ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በግብርና ፣በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች የኢንቬስትመንት 

ልማት ፕሮጄክቶች ላይ ለመሠማራት 28 የኢንቬስትመንት ጥያቄዎች 

ለመስተዳደር ምክር ቤቱ የቀረቡ መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን ፣ መስተዳድር 

ምክር ቤቱ በቀረቡለት ፕሮጄክቶች ላይ ዝርዝር ውይይት ካደረገ በኋላ፣

የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክቶቹ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ 

ውሳኔ አሳልፏል።

በኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክቶቹ የተመዘገው ካፒታል ከ3 ቢሊየን 

9 መቶ 56 ሚሊየን በላይ ብር መሆኑ ተገልጿል ።

Read more
በአጭር ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገን በትብብር መስራት ብቻ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር

 

በአጭር ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገን በትብብር 

መስራት ብቻ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር 

ሆሳዕና፣ሰኔ 9/ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

መርቀው ስራ አስጀምረዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ማዕከሉን መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት በአጭር 

ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገን በትብብር መስራት 

ብቻ ነው ብለዋል። 

በክልሉ ከሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ በተለያዩ ከተሞች 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን 

በመመረቅ ስራ ማስጀመር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በቅርብ ቀን በሌሎች ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

ለምረቃ እንደሚበቁም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

በክልሉ የተያዘው በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ከ15 እስከ 17 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ስራ ለማስጀመር 

እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 

የሚያስፈልገው መተባበር ብቻ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከደባል 

አጀንዳ በመውጣት ለጋራ እድገት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። 

የሆሳዕና ከተማን ከሌሎች ትልልቅ ከተሞች ለማሰለፍ ከ3 እስከ 5 ዓመታት 

ብቻ በቂ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ፣የንግድ ማዕከላት፣

ትምህርት ቤቶች፣የጤና ተቋማት እንዲሁም የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን 

ለማሟላት 10 ቢሊየን ብር በመመደብ መስራት ከተቻለ መሰረታዊ 

ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የህዝብ ትብብር እና ድጋፍ ካለ አካባቢን መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ተወላጆች እና የንግዱ ማህበረሰብ 

ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ለሥራ ክፍት አደረጉ

 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ለሥራ ክፍት አደረጉ

ሆሳዕና ፣ ሰኔ 9 / 2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

የሆሳዕና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውስጡ 

6 ተቋማት የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ 20 የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ 

ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣

የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ .

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣

የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ፣

ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ከተማ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ 

ሆሳዕና ፣ ሰኔ 9/2018) የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሀድያዞን በሆሳዕና ከተማ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል 

በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀው የሆሳዕና ከተማ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከል 15 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል። 

የግብይት ማዕከሉ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን 

አምራቹን እና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን 

በማረጋጋት ረገድ የጎላ ሚና እንዳለውም ተጠቁሟል። 

በማዕከሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ቀርቦ ግብይት

እየተካሔደበት ነው። 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሰኔ 5/2017 ዓም የሆሳዕና ከተማ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ 

የግንባታ ስራ ማስጀመራቸው ይታወሳል። 

በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት 

አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣

የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ፣ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ 

የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በወልቂጤ  ከተማ በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በወልቂጤ  ከተማ

በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ

ሆሳዕና ፣ ሰኔ  8/2018  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በወልቂጤ ከተማ በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ

በተያዘው የትምህርት ዘመን ከሰኔ 8 እስከ 12 / 2018 ባሉት ቀናት 

የ6ኛ እና የ8 ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ይሰጣል።

ይህን ተከትሎም በዛሬው እለት የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና

በተለያዩ ማዕከላት እየተሰጠ ነው።

በክልሉ 46ሺ 151 ወንዶች  እንዲሁም  45ሺ  767  በድምሩ

91ሺ 918  የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና ይወስዳሉ።

 

Read more
በሁሉም ዘርፎች በሚከናወኑ ተግባራት ተደማሪ ድሎች ለማስመዝገብ መስራት ይገባል:-ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በሁሉም ዘርፎች በሚከናወኑ ተግባራት ተደማሪ ድሎች ለማስመዝገብ

መስራት ይገባል:-ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣ሰኔ 7/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ

አፈጻጸም ማጠቃለያ ክልል አቀፍ የአመራር መድረክ

በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በሁሉም ዘርፍ ተደማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ

በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የቤተሰብ ብልጽግናን ማረጋገጥ ልዩልዩ አቅሞችን በማስተባበር የክልሉን

ብሎም የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው ህዝብ እና አመራሩ

 ላደረጉት የላቀ ድጋፍ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሀዊ እንዲሆን ህብረተሰቡ የላቀ

ጥረት ማድረጉን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ኢትዮጵያ መርጣለች፣

አሸንፋለች ሲሉም አብራርተዋል።

የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ

በሁሉም መስክ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ያለ እረፍት መስራት ይገባል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን

ማረጋገጥ አብይ ጉዳይ በማድረግ መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ

አስረድተዋል።

ያለንበት ዘመን እረፍት የሚሰጥ አይደለም ያሉት  ርዕሰ መስተዳድሩ

ለዚህም የአመራሩን ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።

ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሔድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩ እና ከምርጫ

በኋላ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመዳፈር ጥረት ያደረጉ ኃይሎች እንደነበሩ

ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።
ነገር ግን የነዚህ አካላት ሴራ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ድል መደረጉን ጠቅሰዋል።

ፈጥኖ ወደ መደበኛ ስራ ላይ ማተኮር ይጠበቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ

በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

Read more
ተግባራትን በጠንካራ የህዝብ ንቅናቄ በማስፈጸም፣ ለህዝብ ተጠቃሚነት ማደግ መትጋት ይጠበቃል! ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ተግባራትን በጠንካራ የህዝብ ንቅናቄ በማስፈጸም፣ ለህዝብ ተጠቃሚነት ማደግ መትጋት ይጠበቃል! 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

Read more
በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም እየተሻሻለ መጥቷል፤ የአፈጻጸም ልዩነቶች ግን አሁንም ማነቆ ሆነዋል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፤

በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም እየተሻሻለ መጥቷል፤ 

የአፈጻጸም ልዩነቶች ግን አሁንም ማነቆ ሆነዋል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፤ 

ሆሳዕና ፣ሰኔ 3 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራትን 

ወቅታዊ የአፈጻጸም ሁኔታ በበይነ መረብ አማካይነት ዛሬ ገምግመዋል።

በመድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ 

ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ፣ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣

የሚመለከታቸው የክልሉ ካብኔ አባላት፣ የዞኖቾ እና ልዩ ወረዳዎች 

ዋና አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል ።

የአፈጻጸም ግምገማው በፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ፣ 

በመሶብ _የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ዝግጅት፣

በኢትዮ _ኮደርስ ስልጠና፣ በገቢ አሰባሰብ ፣በከተማና በገጠር ኮሪደር ልማት፣ 

በሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች አፈጻጸም፣የኑሮ ውድነትትን ከማረጋጋትና 

የነዳጅ አቅርቦትንና ስርጭትን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑ ተመልክቷል ።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለፁት ፣ 

በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም እየተሻሻለ መጥቷል፤ 

ነገር ግን ከመዋቅር ወደ መዋቅር የሚታዩ የአፈፃፀም ልዩነቶች አሁንም ማነቆ ሆነው ቀጥለዋል። 


የአፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ፣ ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ በተጠያቂነት 

መንፈስ መሥራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜ በሁሉም መስኮች ዕቅዶችን በተሟላ ሁኔታ 

ለማሳካት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

የወልቂጤ ፣ የሆሳዕና፣ የሀላባ ቁሊቶ፣ የቡታጅራ እና የዱራሜ መሶብ _ 

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ቀሪ ስራዎች በፍጥነት አጠናቅቆ፣

በጥቂት ቀናት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ 

መቀጠሉንም ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አመልክተዋል ።

በአጠቃላይ መሶብ _የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ዝግጁ ከማድረግ፣

የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን፣ የኢትዮ _ኮደርስ ስልጠናን ፣ የገቢ አሰባሰብን ፣ 

የሥራ ዕድል ፈጠራን ከማጠናከር አኳያ ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ 

መሆናቸው በመድረኩ ተለይቷል፤ተግባራቱ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም 

አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከከተማና ከገጠር ኮሪደር ልማት አንፃር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት 

ሁሉም መዋቅሮች እንዲረባረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል ።
የኑሮ ውድነትትን ለማረጋጋት የሚያግዙ ሁሉንም አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ 

እንደሚገባ ተመላክቷል ።
ከነዳጅ አቅርቦት አንፃር መሻሻሎች መታየታቸው የተገለፀ ሲሆን የነዳጅ 

ስርጭቱን ከህገ ወጥ ሁኔታዎች በመከላከል ቅድሚያ ለሚያሻቸው ጉዳዮች 

ቅድሚያ መስጠት በሚያስችል መልኩ እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

Read more
ዲጂታል  አገልግሎትን  ተደራሽ  በማድረግ  ዜጎች  ቀልጣፋ  አገልግሎት እንዲያገኙ  ይሰራል - እንዳሻው  ጣሰው (ዶ/ር)

ዲጂታል  አገልግሎትን  ተደራሽ  በማድረግ  ዜጎች  ቀልጣፋ  አገልግሎት 

እንዲያገኙ  ይሰራል - እንዳሻው  ጣሰው  (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ ግንቦት 26፣ 2018 ዲጂታል አገልግሎትን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች

ተደራሽ በማድረግ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይሰራል አሉ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከ260 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ 

የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው 

ሥራ አስጀምረዋል። 

በማዕከሉ 6 የተለያዩ ተቋማት 20 አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ጠቁመው፤ 

በቀጣይ ይበልጥ እየሰፋ ይሄዳል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂውን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ዜጎች የተቀላጠፈ 

አገልግሎት እንዲያገኙ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት 

መስጠት የሚችል የገበያ ማዕከልም መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

መንግስት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን

ለመፍታት ዲጂታል አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው ብለዋል።

ዛሬ በወራቤ ከተማ ተገንብቶ ወደ ስራ የገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቋት በመስጠት የማህበረሰቡን እንግልት 

ያስቀራል ነው ያሉት።

መንግሥት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ የማህበረሰቡን ችግር 

ለመፍታት በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተደምጠዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ መሶብ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ

ሆሳዕና፣ግንቦት 26/2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል

አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ 

በማዕከሉ በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተመላክቷል። 
 

Read more