Skip to main content
ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዱራሜ ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዱራሜ ከተማ

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

ሆሳዕና ፣ ሰኔ 19 / 2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

 እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በከንባታ ዞን በዱራሜ ከተማ ከሰንበት እስከ

ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል

በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀው የዱራሜ ከተማ

ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከል 15 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

በማዕከሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ቀርቦ ግብይት እየተካሔደበት

ሲሆን የግብይት ማዕከሉ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሰኔ

2017 ዓ.ም የዱራሜ ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል የመሰረት

ድንጋይ በማስቀመጥ የግንባታ ስራ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ

አቶ አቡቶ አኒቶ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ

፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣በምክትል ርዕሰ

መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች ፣ የከንባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አቶ አረጋ እሸቱን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Read more
በዛሬው ዕለት በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ላይ በዶክተር ቦጋለች መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተን የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል  የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ክልል አቀፍ ንቅናቄ አሰጀምረናል

በዛሬው ዕለት በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ላይ በዶክተር 

ቦጋለች መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተን የፍራፍሬ 

ችግኞችን በመትከል  የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ክልል አቀፍ 

ንቅናቄ አሰጀምረናል

የኢትዮጵያን መፃኢ ዕጣ ፈንታ ብሩህ እና ቀና

 ለማድረግ ተጨማሪ መደላድል የሚሆኑና ተስፋን የሚዘሩ ችግኞችን 

ተክለናል።


የዛሬ ችግኞች፣ የነገ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ አማራጮች ናቸው፤ 

የተፈጥሮ ሚዛንን ጠብቆ ማቆያ ፀጋዎች ናቸው፤ የዛሬ ችግኞች ፣ ምድርና 

ትውልድ ተዋድደው እንዲቀጥሉ ዋስትናዎች ናቸው።
ተስፋን በጋራ እንትከል!

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የ2018 ዓም የመኸር ወቅት የተቀናጀ የግብርና ስራዎች የንቅናቄ መድረክ እየተካሔደ ነው

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት 

የ2018 ዓም የመኸር ወቅት የተቀናጀ የግብርና ስራዎች 

የንቅናቄ መድረክ እየተካሔደ ነው 

ሆሳዕና፣ ሰኔ 17/2018 ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና 

ሴክተር የ2018 ዓም የመኸር ወቅት የተቀናጀ የግብርና ስራዎች 

የንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ እየተካሔደ ነው።

" የተቀናጀ ግብርና ትጋት ለላቀ ምርታማነት "በሚል መሪ ሀሳብ 

እየተካሔደ ያለው የመኸር ወቅት የግብርናው ሴክተር የንቅናቄ 

መድረክ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና 

እንዳለው ተጠቁሟል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም 

ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አስጀመሩ 

ሆሳዕና፣ሰኔ 17/2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በከምባታ ዞን 

ዱራሜ ከተማ በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል 

ግቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀምረዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ ከ530 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ 

መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። 

እስከ ሐምሌ 25 ፣ 2018 ባሉት ቀናት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች 

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ሀገርን ከሚለውጡ ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ 

ችግሮችን ለመቅረፍ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ለምግብነት፣ለመድሀኒትነት፣ለቁሳቁስ መስሪያነት እና 

ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን 

ተናግረዋል። 

በተለያዩ ጊዜያት እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የጽድቀት መጠን እየጨመረ 

ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የክልሉ ህዝብ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር የውሃ 

አካላት መጨመር ስለመስተዋሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። 

የክልሉ ህዝብ እስከ ሐምሌ 30/2018 በዘመቻ ለሚካሔደው የአረንጓዴ 

አሻራ ፕሮግራም ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ የክልል፣የዞን እና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች 

ተሳትፈዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ለሥራ ክፍት አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)  በሀላባ ቁሊቶ ከተማ 

አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው 

ለሥራ ክፍት አደረጉ

ሆሳዕና ፣ ሰኔ / 2018 ዓ.ም ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሀላባ ቁሊቶ ከተማ 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

የሀላባ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውስጡ 8 ተቋማት 

የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ 20 የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ 

ተገልጿል።

Read more
በሁሉም ዘርፍ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት እንዲኖረው መስራት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በሁሉም ዘርፍ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 

የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት እንዲኖረው መስራት ይገባል:-

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሰኔ 16/ 2018 :- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓም 

የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ 

በይፋ ተጀምሯል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

የአንዲትን አረጋዊት ቤት ግንባታ ባስጀመሩበት ጊዜ እንደገለጹት 

በክልሉ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የአንድ ወቅት ብቻ ሊሆን አይገባም ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ ስራው ዘላቂነት እንዲኖረው ማተኮር ተገቢ ስለመሆኑም 

አጽንኦት ሰጥተዋል። 

አረጋውያንን መርዳት፣የአካባቢ ችግርን መፍታት ካለን እያካፈልን የዜጎችን 

ተጠቃሚነት ማሳደግ የህሊና እርካታ እንደሚሰጥ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በክልሉ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1ሺ በላይ ቤቶች እንደሚገነቡ የገለጹት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የቤቶች ደረጃ ዲዛይን መጠናቀቁን አስታውቀዋል። 

በዘርፉ የሚካሔደውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬታማ ለማድረግ መላው ህዝብ፣

አመራሩ እና ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) የ2018 ዓ.ም 

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመሩ

የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው( ዶ/ር ) 

የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ 

የአንዲት አረጋዊያን ቤት ግንባታን በማከናወን ነው ያስጀመሩት።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው ልዑካን 

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ አከናውነዋል።

በክልሉ ዛሬ በሚጀመረው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 

በ15 የስምሪት መስኮች ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል።

Read more
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን ይሁንታ ወደ ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን ይሁንታ ወደ 

ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ሰኔ 16/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓም 

የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም 

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን ይሁንታ ወደ 

ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል ብለዋል። 

በጎነት የመስጠት እና የማካፈል መርህ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በተለይ ተማሪዎችን ማስተማር፣በስነ ምግባር እንዲታነጹ በማድረግ 

ለቀጣዩ አመት ዝግጁ እንዲሆኑ መደገፍ ይገባል። 

ከእውቀት ሽግግር ባለፈ ሀብትን እና ጊዜን በማካፈል የበጎ ፈቃድ 

አገልግሎት ስራ ማከናወን ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም 

የሁሉንም አካላት ተሳትፎ እና ትብብር ይጠይቃል ብለዋል። 

የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ እሴትን በማጎልበት የሰዎችን ስሜት መረዳት 

የበጎነት መገለጫ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የድህነትን ቅነሳ አንዱ አካል ነው ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ መተባበርን እና አብሮነትን የምናጸናበትን እድል 

የሚፈጥር ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል። 

በመረዳዳት ውስጥ የጋራ ትርክትን የምንፈጥርበት ነው ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን 

ይሁንታ ወደ ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር መትጋት ይገባል ብለዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር የ2018 ዓ.ም 

የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ 

መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

ሆሳዕና ሰኔ 16 / 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የአንዲት አረጋዊያን ቤት በማፍረስ ግንባታ እንደሚያስጀምሩ 

ይጠበቃል።

የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎፍቃድ አገልግሎት " በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " 

በሚል መርህ በ15 የስምሪት መስኮች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሞአል።

Read more
ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ነው :- ርዕ ሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር

ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን

ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ነው :- ርዕ ሰመስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር

ሆሳዕና፣ሰኔ 11/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካውንስል

የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሬሽንና የቀዳማይ የልጅነት

ፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

እንደገለጹት የምግብ ስርዓት ሽግግርና ፍኖተ ካርታ አብይ ዓላማ ያደገና

ዘላቂ የምግብ ስርዓት መፍጠር ነው ብለዋል።

ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ስራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያመላከቱት

ርዕሰ መስተዳድሩ የግብርናው ዘርፍ ሲሻሻል የምናልማቸውን ግቦች ማሳደግ

እንደሚያስችልም አስረድተዋል።

ህጻናት በልጅነታቸው በሚመገቡት ፣ በሚያዩት ፣በሚሰሙት እና በሚዳስሱት

ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ ያድርባቸዋል ብለዋል።

በሁሉም ዘርፍ ጤናማና ንቁ ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን ላይ

በትኩረት መስራት ተገቢ ስለ መሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በትውልድ ግንባታ ላይ መስራት ለሀገር ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ

ከፍተኛ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።

Read more